am_tn/ezk/32/26.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በሲኦል ስለሚገኙ ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል

ሞሳህ…ቶቤል

እነዚህ ስሞች በሕዝቅኤል 27፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡

በሰይፍ የተገደሉ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚወክለው ጦርሜዳን ነው፡፡ "በጦር ሜዳ የተገደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሽብራቸውን ወደ ህያዋን ምድር አመጡ

ሰዎች እንዲፈሩ ማድረግ የተገለጸው አንደን አካል ወደ እነርሱ እንደ ማምጣት ድርጊት ተደርጎ ነው፡፡ "ሽብር" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ መልኩ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በህያዋን ምድር የሚገኙትን ሁሉ አሸበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም… የህያዋን ምድር

በሕዝቅኤል 32፡25 ላይ የሚገኘው "ሁሉም… የህያዋን ምድር" የሚለው እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በደላቸው በአጥንቶቻቸው ላይ

ምንም እንኳን አንድ ሰው ጋሻዎቻቸው በሞታቸው እንደሚጋርዳቸው ቢያስብም፣ የጦረኞች በደል አካላቸውን ሸፍኗል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በህያዋን ምድር የጦረኞች ሽብር ነበሩ

"በህይወት ሳሉ፣ ጦረኞችን በጣም ያስፈራሉ"

በህያዋን ምድር

እነዚህ ጦረኞች ይኖሩበት የነበረበት ጊዜ የተገለጸው ስፍራ ተደርጎ ነው፡፡ "በህይወት በነበሩበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)