am_tn/ezk/32/22.md

3.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በሲኦል ስለሚገኙ ህዝቦች መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ምክንያቱም ያህዌ ለሕዝቅኤል ለወደፊቱ ጊዜ፣ ወይም ስለአሁን ጊዜ ወይም ስለ መጪው ጊዜ የሚያሳየው ለእነዚህ ቁጥሮች እና ለተከታዮቹ ቁጥሮች ተስማሚ ሊሆን ይችላል፡፡

አሦር ከመላው ጉባኤዋ ጋር በዚያ ናት

የአሦር ምድር በሴት ተገልጻለች፡፡ "የአሦር ህዝብ እና መላው ሰራዊቷ በዚያ በሲኦል አሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሷ ጉባኤ

"የእርሷ ሰዎች ሁሉ በአንድነት"

ሁሉም በሰይፍ ተገደሉ

"ሰይፍ" የሚለው ቃል ሰዎችን ለመግደል ሰይፍ ለሚጠቀሙ ወታደሮች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወታደሮች እነርሱን በሙሉ ለመግደል ሰይፍ ተጠቅመዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በጉድጓዱ ስርጓድ ተጨመሩ

"ጉድጓዱ" የሚለው የሚያመለክተው መቃብርን ነው፣ ምክንያቱም መቃብር ወደ ሞት ዓለም መግቢያ ተደርጎ ይታሰብ ነበር፣ እንደዚሁም ደግሞ ጉድጓድ ያንን ዓለም ይወክላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 31፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ የወደቁት፣ የተገደሉት ሁሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በጦርነት የተገደሉ ተላቶች ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በሰይፍ የወደቁ

እዚህ ስፍራ "መውደቅ" የሚለው ቃል "ሞት" ለሚለው ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

በህያዋን ምድር ይሽብር የሚያመጡ

"ሽብር" የሚለው ረቂቅ ስም "ፍርሃት" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በህይወት ባለሁበት ጊዜ ሰዎች እጅግ እንዲፈሩ ምክንያት የነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የህያዋን ምድር

ይህ የሚወክለው በህይወት የነበሩተን ሰዎች ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)