am_tn/ezk/32/17.md

3.4 KiB

እንዲህም ሆነ

እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅማሬ ለማመልከት ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህንን ለማድረግ የሚችልበት መንገድ ካለው እዚህ ስፍራ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡

በአስራ ሁለተኛው አመት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን ወደ ባቢሎን በወሰዱ በአስራ ሁለተኛው አመት ሆነ ወይም 2) ይህ ባቢሎናውያን ዮአኪንን ወደ ባቢሎን በወሰዱ በአስራ ሁለተኛው አመት ሆነ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እነርሱን አዋርዳቸው - እርሷ እና የግርማዊ ህዝቦቿን ሴት ልጇቿ

እግዚአብሔር ለህዝቅኤል ይህ ይሆን ዘንድ ትንቢታዊ ትዕዛዝ እየሰጠው ሊሆን ይችላል

የእርሷ

ዳግም፣ የግብጽ ምድር በሴት ተገልጻለች

የግርማዊ ህዝቧቿ ሴት ልጆች

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "የሃያላን ሀገሮች ህዝቦች" ወይም 2) "ሌሎች ሀያልን ሀገሮች"

የታችኛው ምድር

"ከምድር በታች የሚገኝ ስፍራ፡፡" ሰዎች ሲሞቱ፣ ምድር ውስጥ ይቀበራሉ፡፡ ስለዚህ "ወደታች ከምድር በታች… አውርዳቸው" ማለት "ግደላቸው" ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጉድጓድ ከወረዱት ጋር

"ከሌሎች ከሞቱት ከእያንዳንዳቸው እና ወደ አፈር ከገቡት ጋር"

ጉድጓዱ

"ጉድጓዱ" የሚለው የሚያመለክተው መቃብርን ነው፣ ምክንያቱም መቃብር ወደ ሞት ዓለም መግቢያ ተደርጎ ይታሰብ ነበር፣ እንደዚሁም ደግሞ ጉድጓድ ያንን ዓለም ይወክላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 31፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)