am_tn/ezk/32/15.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የግብጽን ምድር የተረሳች/የተተወች በማደርግበት ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የግብጽን ምድር ማንም የማይኖርበት በማደርግበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱ ፍሬያማነቷን ባጣች ጊዜ

"አገሪቱ ሀብቷን እንድታጣ ባደረግሁ ጊዜ"

በውስጧ የሚኖሩትን በጠቃሁ ጊዜ

እዚህ ስፍራ ማጥቃት የሚለው ሀሳብ የሚወክለው ማጥፋትን/መደምሰስን ነው፡፡ "በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ ባጠፋሁ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሷ ውሰጥ… በእርሷ ላይ

በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቋንቋ አገራትን እና ምድርን በሴት ጾታ መግለጽ የተለመደ ነበር፡፡ "በእርሷ ውስጥ.. በእርሷ ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ እርሱ ያህዌ እንደሆነ ሰዎች ያውቃሉ ሲል፣ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የህዝቦች ሴት ልጅ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "የሌሎች አገራት ሴቶች" ወይም 2) "የሌሎች አገራት ሰዎች"

በግብጽ ላይ፣ በእርሷ አእላፋት/ብዙዎች ላይ

"ስለ ግብጽ፣ ስለ እርሷ አእላፋት/ብዙዎች" ወይም "በግብጽ ላይ ስለሚደርስ ጥፋት፣ በአእላፍቶቿ/በበርካታ ሰዎቿ ላይ ስለሚደርስ ጥፋት"