am_tn/ezk/32/13.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ከብዙ ውኆች አጠገብ

"ብዙ ውሃ በሚገኝበት ስፍራ"

የሰው እግር ውኆችን አያናውጥም

እዚህ ስፍራ እግር ለሰው ሁለንተና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "ከእንግዲህ ሰዎች በእግራቸው ውኆችን አይበጠብጡም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ውኆችን መበጥበጥ

ንጹሁን ውሃ ማደፍረስ

የከብቶች ኮቴ ይበጠብጣቸዋል

ኮቴ ለከብቶች ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "ከብቶች በኮቴያቸው ይበጠብጧቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም ውሃቸውን አጠራለሁ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ውሃውን የጠራ አደርገዋለሁ" ወይም 2) "ውሃውን ንጹህ አደርጋለሁ፡፡" ማንም ውሃውን በማይበጠብጠው ጊዜ፣ ዝቃጩ ከታች ይቀመጣል፣ ውሃውም ንጹህ ይሆናል"

ወንዛቸው እንደ ዘይት እንዲፈስ አደርጋለሁ

ዘይት በቀስታ እና በእርጋታ ይፈሳል፡፡ "ወንዞቹ እንደ ዘይት በቀስታ እንዲፈሱ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)