am_tn/ezk/32/11.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለፈርኦን መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ በአንተ ላይ ይመጣል

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚወክለው ሰራዊትን ነው፡፡ "የባቢሎን ሰራዊት ንጉሥ አንተን ያጠቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ተዋጊ ለህዝብ ሽብር ይሆናል

"ሽብር" የሚለው ረቂቅ ስም "አሸባሪ" ወይም "አስፈሪ" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እያንዳንዱ ተዋጊ ህዝብን ያሸብራል" ወይም "ከእነርሱ እያንዳንዱ ህዝቡ እንዲፈራ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የግብጽን ኩራት ከንቱ ያደርጋል

"መኩራት" የሚለው ረቂቅ ስም "ኩራት" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከእንግዲህ ግብጻውያን እንደይኮሩ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አእላፋቶቿን ያጠፋል

እዚህ ስፍራ "ሁሉ" የሚለው ምናልባት የንጉሡን ብዙ ቁጥር ያለውን ወታደር፣ እና ምናልባትም ሌሎች ሰዎችንም ጨምሮ ሊሆን ይችላል፡፡ "በግብጽ የሚኖሩ አያሌ ሰዎችን ይገድላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)