am_tn/ezk/32/01.md

3.5 KiB

እንዲህም ሆነ

እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅማሬ ለማመልከት ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህንን ለማድረግ የሚችልበት መንገድ ካለው እዚህ ስፍራ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡

በአስራ ሁለተኛው ወር… በወሩ መጀመሪያ

ይህ በዕብራውያን አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው እና የመጨረሻው ወር ነው፡፡ የመጀመሪያው ቀን በየካቲት መጨረሻ አቅራቢያ ነው፡፡ (የዕብራውያን ወራት እና ተከታታይ ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

በአስራ ሁለተኛው ወር

ይህ የሚያመለክተው የንጉሥ ዮአኪንን ግዛት አስራ ሁለተኛ አመት ነው፡፡ "በንጉሥ ዮአኪን ስደት አስራ ሁለተኛ አመት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተከታታይ ቁጥሮች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ከፍ ማድረግ

"መዘመር"

አንተ ልክ እንደ ደቦል አንበሳ ነህ… በባህር ውስጥ እንደሚኖር አውሬ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እርሱ እንደ አንበሳ ነኝ ብሎ ያስብ ነበር፣ ነገር ግን እርሱ በእርግጥ እንደ አውሬ ብቻ ነበር፣ ወይም 2) እርሱ እንደ አንበሳ እና አውሬ ነበር፡፡

በአገራት መሃል እንደ ደቦል አንበሳ

አንበሶች ከሌሎች እንስሳት ይልቅ ጠንካራ እንደሆኑ፣ ግብጽ ከሌሎች አገራት ይልቅ ጠንካራ ነበረች፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በባህሮች ውስጥ እንዳለ አውሬ

ፈርኦን ሀያል ነበር፣ ነገር ግን እርሱ በውሃ ውስጥ እንዳለ እንደዚህ አውሬ ለሌሎች ችግር ምክንያት ነበር፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አውሬ

አውሬ ትልቅ እና አደገኛ እንስሳ ነው፡፡ ይህኛው አዞ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 29፡3 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡