am_tn/ezk/30/25.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እግዚአብሔር ስለ ግብጽ እና ባቢሎን ሰራዊቶች የንጉሦቻቸው ክንድ እንደሆኑ አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እንደዚሁም የባቢሎንን ሰራዊት ሌሎችን ለማጥቃት እንዲችሉ እርሱ ሰይፍ እነዳለውና ሰይፉንም በባቢሎናውያን ንጉሥ እጅ ላይ እንዳስቀመጠው አድርጎ ይናገራል፡፡ (ምሳሌዎች የሚለውን መልከቱ)

እኔ የባቢሎን ንጉሥን ክንዶች አጠነክራለሁ

እዚህ ስፍራ "ክንዶች" የሚለው ለሰራዊቱ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "የባቢሎንን ንጉሥ ሰራዊት አበረታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የፈርኦን ክንዶች በሚወድቁበት ጊዜ

እዚህ ስፍራ "የፈርኦን ክንዶች" የሚለው ለእርሱ ሰራዊት ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "በሚወድቁበት ጊዜ" የሚለው የሚወክለው መድከምን ነው፡፡ "ነገር ግን የፈርኦን ሰራዊት ጠላት ማሸነፍ የማይችሉ ይሆናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም እነርሱ

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ተከታዩን ሊሆን ይችላል 1) "ግብጻውያንን" ወይም 2) "ያህዌ ያደረገውን የሰሙትን ሰዎች ሁሉ"

ከዚህ ጋር እርሱ የግብጽን ምድር ያጠቃል

"እናም የባቢሎን ንጉሥ በእኔ ሰይፍ የግብጽን ምድር ያጠቃል"

ግብጽን በህዝብ መሃል እበትናለሁ ደግሞም በምድር ሁሉ እበትናቸዋለሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይህ በህዝቅኤል 12፡15 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)