am_tn/ezk/30/22.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እግዚአብሔር ስለ ፈርኦን ሰራዊት እንደ ተሰበረ ክንድ አድረጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የባቢሎንን ሰራዊት ማጠንከርን የባቢሎን ንጉሥን ክንድ እንደ ማጠንከር አድርጎ ይናገራል፡፡

ጌታ ያህዌ ይህን አለ/ያህዌ እንዲህ አለ

ይህ በሕዝቅኤል 3፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ጠንካራው እና የተሰበረው ሁለቱም

"ጤነኛ የሆነው ክንድ እና አስቀድሞ የተሰበረው ክንድ ሁለቱም"

ሰይፉ ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ

"ከፈርኦን እጅ ሰይፉን መትቼ አስጥለዋለሁ"

ግብጽን በህዝቦች መሃል እበትናለሁ፣ እናም እነርሱን በምድር ዙሪያ እበትናቸዋለሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በሕዝቅኤል 12፡15 ላይ ተመሳሳይ ሆነው ሀረግ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምድር ዙሪያ

"ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ"

የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ

"የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች ጠንካራ አደርጋለሁ"

በባቢሎን ንጉሥ ፊት ያቃስታል

"የባቢሎን ንጉሥ ግብጽን ሊያጠቃ ሲመጣ፣ ፈርኦን ያቃስታል፡፡"

ማቃሰት

ማቃሰት ሰዎች ብዙ ስቃይ ሲደርስባቸው ወይም ሲያጣጥሩ የሚያሰሙት ድምጽ ነው፡፡

የሚያጣጥር ሰው ማቃሰት

"ሰው እያጣጣረ ሲያቃስት" ወይም "እያጣጣረ እንደሚገኝ ሰው"