am_tn/ezk/30/20.md

3.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የፈርኦንን ሰራዊት ደካማ እንደሚያደርግ የሚናገረው፣ የፈርኦንን ክንድ እንደ መስበር እና የተሰበረው የፈርኦን ክንድ ፈውስ እንደሌለው እንደዚህም ሰራዊቱ ዳግም ጠንካራ ሊሆን እንደማይችል አድርጎ ነው፡፡ (ምሳሌዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም እንዲህ ሆን

ይህ ሀረግ እዚህ ስፍራ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅማሬ ለማመልከት ነው፡፡ ቋንቋችሁ ይህን ለማድረግ መንገድ ካለው፣ እዚህ ስፍራ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

አስራ አንደኛው አመት

ይህ ንጉሥ ዮአኪን በስደት ወደ ባቢሎን በሄደ አስራ አንደኛው አመት ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 26፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ ሰባተኛ ቀን

"በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፡፡" ይህ በዕብራውያን የወር አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው፡፡ ሰባተኛው ቀን በምዕራባዊያን አቆጣጠር ሚያዚያ መጀመሪያ አካባቢ ነው፡፡ (የዕብራውያን ወሮች እና ተከታታይ ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔ የፈርኦንን ክንድ ሰብሬያለሁ

እዚህ ስፍራ "ክንድ" የሚወክለው የንጉሥን ጠንካራ ሰራዊት ነው፡፡ (ምሳሌዎች እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እነሆ

"ቀጥሎ የምናገረው እውነተኛ እና ትልቅ ነገር ስለሆነ ትኩረት ስጡት"

ክንዱ አልተጠቀለለም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ክንዱን ማንም አላሰረውም" ወይም "ማንም ክንዱን አልጠቀለለውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም እንዲፈወስ በጨርቅ/ፋሻ አልታሰረም

እዚህ ስፍራ "እንዲፈወስ በጨርቅ/ፋሻ መጠቅለል" የሚለው የሚያመለክተው አጥንቱ መልሶ እንዲጠገንእና እንዲፈወስ ክንዱን ጠበቅ አደርጎ በፋሻ መጠቅለልን ነው፡፡