am_tn/ezk/30/15.md

3.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ያህዌ ስለ ግብጽ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፡፡

በፔሉሲየም ላይ ቁጣዬን አፈሳለሁ

እዚህ ስፍራ "ቁጣዬን አፈሳለሁ" የሚለው የሚገልጸው ከታላቅ ቁጣው የተነሳ ህዝቡን መቅጣቱን ነው፡፡ "ፔሉሲየምን በታላቅ ቁጣ እቀጣለሁ" ወይም "እጅግ ከመቆጣቴ የተነሳ፣ ፔሉሲየምን እጅግ አድርጌ እቀጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፔሉሲየም

በሰሜናዊ ግብጽ የምትገኝ የምሽግ ከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የቴቤስን አእላፋት/አያሌ እቆርጣለሁ

እዚህ ስፍራ "መቁረጥ" የሚለው የሚገልጸው ሰዎችን መግደልን ነው፡፡ "በቴቤስ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እገድላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቴቤስ

ይህች የደቡባዊ ግብጽ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡14 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ፔሉሲየም በታላቅ ስቃይ ውስጥ ትገባለች

እዚህ ስፍራ "ፔሉሲየም" በፔሉሲየም ከተማ ዙሪያ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን፤ "በታላቅ ስቃይ ውስጥ መሆን" የሚለው "ተሰቃዩ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ " የፔሉሲየም ሰዎች እጅይ ይሰቃያሉ" ወይም " የፔሉሲየም ሰዎች ከፍተኛ ስቃይ ያገኛቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ቴቤስ ትንኮታኮታለች/ትሰባበራለች

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጠላት የቴቤስን ቅጥሮች እና ግንቦች ይሰባብራል" ወይም "ጠላት ቴቤስን ያጠፋታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሜምፊስ ጠላት በየቀኑ ይገጥማታል

እዚህ ስፍራ "የጠላት መግጠም" የሚወክለው ጠላት ማየትን ወይም የጠላትን መኖር ነው፡፡ የከተማይቱ ስም በከተማይቱ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "የሜምፊስ ሰዎች በየዕለቱ ጠላት ይገጥማቸዋል" ወይም "ጠላት በየእለቱ የሜምፊስን ሰዎች ይዋጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሜምፊስ

ሜምፊስ በግብጽ በጣም ትልቅ ከተማ ነበረች፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 30፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡