am_tn/ezk/30/13.md

1.8 KiB

ጌታ ይህዌ እንዲህ ይላል

"እንዲህ" የሚለው ቃል ቀጥሎ የሚሆነውን ያመለክታል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡5 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ዋጋ ቢስ ለሆኑ ጣኦቶች ፍጻሜ አመጣለሁ

"ዋጋ ቢስ የሆኑ ጣኦቶችን አጠፋለሁ"

ሜምፊስ

ሜምፊስ በግብጽ ውስጥ የሚገኝ ትልቅ ከተማ ነበር፡፡ በአሁኗ ካይሮ አቅራቢያ ትገኝ ነበር፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በግብጽ ምድር የሚገኝ ልዑል /የግብጽ ልዑል

"በግብጽ ምድር ከፍተኛ መሪ"

በግብጽ ምድር ሽብር እሰዳለሁ

እዚህ ስፍራ "በምድሪቱ ሽብት መስደድ" የሚለው የሚወክለው የምድሪቱ ሰዎች በጣም እንዲፈሩ ማድረግን ነው፡፡ "የግብጽ ሰዎች በጣም እንዲፈሩ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጳትሮስ

ይህች በደቡብ ግብጽ የምትገኝ አካባቢ ነበረች

በጣኔዎስ እሳት አነዳለሁ

"ጣኔዎስን በእሳት አቃጥላለሁ"

ጣኔዎስ

ጣኔዎስ በግብጽ ትገኝ የነበረች ሌላዋ ትልቅ ከተማ ነበረች

በቴቤስ የፍርድን ተግባር እፈጽማለሁ

"የፍርድን ተግባር" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው ቅጣትን ነው፡፡ "ቴቤስን እቀጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ቴቤስ

ይህች የደቡባዊ ግብጽ ዋና ከተማ ነበረች