am_tn/ezk/30/08.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ያህዌ ስለ ግብጽ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፡፡

ከዚያም እነርሱ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ከዚያም ሰዎች" ወይም 2) "ከዚያም ግብጻውያን"

እነርሱ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ ያውቃሉ

ያህዌ እርሱ ብቻ የበላይ እና ስልጣን ያለው መሆኑን እንደሚያውቁ እያመለከተ ነው፡፡ ይህ ተመሳሳይ ሀረግ በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እውነተኛው ብቸኛ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ ያውቃሉ" ወይም "እኔ፣ ያህዌ ሉዓላዊ ሀይል እና ስልጣን እንዳለኝ ይረዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በግብጽ ላይ እሳት ሳስቀምጥ

እዚህ ስፍራ "በግብጽ ላይ እሳት ማስቀመጥ" የሚለው የሚወክለው ወደ ግብጽ ለጥቃት ወታደሮችን መላክ እና እሳት መለኮስን ነው፡፡ "ወደ ግብጽ ግብጽን እንዲያቃጥሏት ወታደሮችን ስልክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ረዳቶቿ ሁሉ ተደምስሰዋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የግብጽን አጋሮች ሁሉ እደመስሳለሁ" ወይም "ወታደሮች ግብጽን የሚረዱትን ሁሉ ሲደመስሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መልዕክተኞች አርፈው የተቀመጡትን ኩሽ ለማሸበር ከእኔ ፊት በመርከብ ይወጣሉ

መልዕክተኞች በወሬው የሚደናገጡትን፣ የግብጽን ጥፋት ወደ ኩሽ ይዘው ያመጣሉ

አርፈው የተቀመጡ ኩሽን ለማሸበር

"ተረጋግተው የተቀመጡትን ኩሽ ለማስፈራራት"

በግብጽ የጥፋት ቀን በመሃላቸው ጭንቀት ይሆናል

"ጭንቀት" የሚለው ረቂቅ ስም እና "ጥፋት" የሚሉት "መከራ" እና "ቅጣት" በሚሉ ቃላት ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "የኩሽ ሰዎች ግብጽን በምቀጣበት ቀን መከራ ይቀበላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

እዚህ ስፍራ "እነሆ" የሚለው ቃል ቀጥሎ የሚሆነውን ያጎላል፡፡ "በእርግጥ!" ተብሎም ሊተረጎም ይችላል፡፡

ይህ እየመጣ ነው

"ይህ" የሚለው የሚያመለክተው ግብጽ በምትቀጣበት ጊዜ ኩሽ አብሮ ሲቀጣ የሚደርስበትን "ታላቁን ስቃይ" ወይም "ታላቅ ሀዘን" ነው፡፡