am_tn/ezk/29/19.md

1.8 KiB

እነሆ!

"ተመልከት!" ወይም "አድምጥ!" ይህ ቃል ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት ይሰጣል፡፡"ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር እሰጣለሁ

ያህዌ የባቢሎን ሰራዊት ግብጽን እንዲያሸንፍ ማድረጉን፣ እግዚአብሔር ግብጽን ለናቡከደነጾር እንደሚሰጥ አድርጎ ይናገራል፡፡ "የናቡከደነጾር ሰራዊት፣ የባቢሎን ንጉሥ ግብጽን እንዲያሸንፍ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የሰራዊቱ ደሞዝ ይሆናል

እግዚአብሔር ስለእነዚህ ነገሮች፤ የናቡከደነጾር ሰራዊት ለእርሱ በመስራታቸው የሚከፍላቸው ነገር እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ "የእርሱ ሰራዊት እነዚህን ነገሮች ክፍያው እንደሆነ አድርጎ ይቀበላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)