am_tn/ezk/29/15.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል፣ ስለ ፈርኦን መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል

ከመንግሥቱ አናሳ

እዚህ ስፍራ "አናሳ" የሚለው የሚወክለው ከሁሉም ዝቅ ያለ ዋጋ ስፍራ የያዘ መሆኑን ነው፡፡ "ከመንግሥታት ዝቅተኛው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከመንግሥታት መሃል ከእንግዲህ ወዲያ አይነሳም

እዚህ ስፍራ "መነሳት" የሚለው የሚወክለው ጠቃሚ መሆንን ነው፡፡ "ከእንግዲህ ወዲያ ዳግም በመንግስታት መሃል ጠቃሚ አይሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ አጠፋቸዋለሁ

"እኔ ትንሽ አደርጋቸዋለሁ፡፡" እዚህ ስፍራ "እነርሱን አጠፋለሁ" የሚለው የሚወክለው ግብጽን ደካማ እና ጥቅም የሌላት ማድረግን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ግብጻውያን ለእስራኤል ቤት የኩራት ምክንያት አይሆኑም

"ኩራት" የሚለው ረቂቅ ስም "መታመኛ" ወይም "መደገፊያ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የእስራኤል ቤት ከእንግዲህ በግብጻውያን አይታመንም/አይደገፍም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የሚወክለው የእስራኤልን ሰዎች ነው፡፡ "የእስራኤልን ሰዎች" ወይም "የእስራኤል ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ እስራኤል ለፈጸመው በደል ማስታወሻ ይሆናሉ

ግብጽ እንዴት ማስታወሻ እንደምትሆን በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማስታወሻ" እና "ኃጢአት/በደል" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "አስታውስ" እና "ኃጢአት" በሚሉ ግሶች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "እኔ በግብጽ ላይ ያደረግኩትን ሲመለከት እስራኤል እንዴት አስራኤልን እንደበደለ ያስታውሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

እነርሱ ለእርዳታ ወደ ግብጽ ሲመለሱ

እዚህ ስፍራ "ለእርዳታ …መመለስ" የሚለው "እርዳታ …መጠየቅ" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ግብጻውያን እንዲረዷቸው በጠየቁ ጊዜ ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)