am_tn/ezk/29/08.md

4.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል፣ ስለ ፈርኦን መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል

እነሆ!

"ተመልከት!" ወይም "አድምጥ!" ይህ ቃል ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት ይሰጣል፡፡ ይህ ጌታ ለፈርኦን ያለው መልዕክት ነው፡፡ "ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በአንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" ለጦርነት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ሲሆን/፣ "በአንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ" የሚለው የጠላት ሰራዊት ግብጽን ለመውጋት ለመምጣቱ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "ጠላቶችህ አንተን ለመውጋት እንዲመጡ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ላይ ሰይፍ

"አንተ" የሚለው ቃል ግብጽን ያመለክታል፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

ከአንተ ሰውንና አራዊትን በአንድነት እቆርጣለሁ

እዚህ ስፍራ "ሰውንና አራዊትን እቆርጣለሁ" የሚለው ሰዎችንና እንስሳትን ለማጥፋት የዋለ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር የጠላት ሰራዊት ይህንን እንዲያደርግ በማድረግ ይፈጽመዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ በአንተ እና በወንዝህ ላይ ተነስቻለሁ

"አንተ" የሚለው ቃል ፈርኦንን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር ፈርኦንን በወንዝ ውስጥ እንደሚኖር አውሬ ይገልጸዋል፡፡

የግብጽን ምድር ሰው የማይኖርበት እና የጠፋ አደርገዋለሁ

"ግብጽን ለጥፋት እና ውድመት ሀይል እሰጣለሁ" ሰው የማይኖርበት እና የጠፋ የሚሉት የተገለጹት በግብጽ ላይ ሀይል እንዳላቸው ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ "ግብጽ ሰው የማይኖርባት እና የጠፋች እንድትሆን አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የጠፋ ምድር ትሆኛለህ

እዚህ ስፍራ "አንተ" ፈርኦንን ሲያመለክት የሚገዛትን ግብጽንም ይወክላል፡፡ "አገርህ የጠፋ ምድር ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከሚግዶል እስከ ሲና ደግሞም እስከ ኩሽ ድንበሮች ድረስ

ይህ መላውን ግብጽ ያመለክታል፡፡ እነዚህ ስፍራዎች የት እንደሆኑ ይበልጥ በግልጽ ሊጻፉ ይችላል፡፡ "በሰሜን ከሚግዶል በደቡብ እስከ ሲና ደግሞም ሩቅ በስተ ደቡብ እስከ ኩሽ ድንበር ድረስ በመላው ግብጽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጽንፍ/ከዳር እስከ ዳር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሚግዶል

ይህ በግብጽ በስተሰሜን ዳርቻ የሚገኝ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ሲና

ይህ በደቡባዊ ግብጽ የሚገኝ ከተማ ስም ነው፡፡ አሁን አስዋን ተብላ ትጠራለች፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የኩሽ ድንበሮች

እነዚህ የኩሽ ድንበሮች በሲና በስተ ደቡብ ነበሩ፡፡ አንዳንድ ቅጂዎች በዘመናችን ከግብጽ በስተደቡብ የሚገኙትን አገራት በመጠቀም ሱዳን ወይም ኢትዮጵያ ይላሉ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)