am_tn/ezk/29/06.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል፣ ስለ ፈርኦን መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ ይህንን ሲናገር ሰዎች እርሱ ያህዌ እንደሆነ ያውቃሉ፤ ሰዎች እርሱ ብቻ ሉዓላዊ/የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሃይል ያለው መሆኑን እንደሚያውቁ እያመለከተ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እኔ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ፣ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ፣ ያህዌ ሉዓላዊ ሀይል እና ስልጣን እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ የሸምበቆ አገዳ ነበሩ

"እነርሱ" የሚለው ቃል የግብጽን ነዋሪዎች ያመለክታል፡፡ የሸምበቆ አገዳ አስተማማኝ አይደለም ምክንያቱም በቀላሉ ተሰባሪ ነው፡፡ ያህዌ እነርሱን እንደ ሸምበቆ አገዳ የሚገልጻቸው፣ ግብጻውያን በጦርነት ወቅት እነርሱን እንዲረዱ ስለጠየቋቸው እና ግብጻውያን ስላልረዷቸው ነው፡፡ "እነርሱ እንደ ሸምበቆ አገዳ ሊታመኑባቸው የማይቻል ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሸምበቆ

በውሃ አጠገብ የሚበቅል እና ረጅም ሳር የመሰለ ተክል ነው

አገዳ

ረጅም በትር የሚመስል የቄጤማው ክፍል ነው፡፡ ሰዎች እንደ በትር ሊጠቀሙባቸው ሲችሉ ነገር ግን እንደ እንጨት በትር ቄጤማ ጠንካራ ባለመሆኑ በቶሎ ተሰባሪ ነው፡፡

እነርሱ በእጃቸው እናንተን ሲይዟችሁ

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በግብጻውያን ላይ መታመናቸው ተሰባሪ የሸምበቆ ምርኩዝ እንደመደገፍ አድርጎ ይናገራል፡፡ "እነርሱ በአንተ ሲታመኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አንተን ሲደገፉ

"እነርሱ" የሚለው ቃል እስራኤላውያንን ሲይመለክት "አንተ" የሚለው ፈርኦንን ወይም ፈርኦንን እና ግብጽን ያመለክታል፡፡

እግራቸው እንዳይጸና አደረግህ

ግብጽ እስራኤላውያንን ስላልረዳች፣ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ባቢሎናውያንን መቋቋም አልቻሉም፡፡ እግዚአብሔር ራሳቸውን መከላከል አለመቻላቸውን የገለጸው እግራቸው መጽናት እንዳልቻለ አድርጎ ነው፡፡ "እግራቸው መጽናት እንዳልቻለ ሰው አደረግሃቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)