am_tn/ezk/29/04.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል፣ ስለ ፈርኦን መልዕክት መስጠቱን፤ ፈርኦን በውሃ ውስጥ እንደሚኖር አውሬ መሆኑን እና የግብጽ ሰዎች አሳ መሆናቸውን መናገሩን ቀጥሏል፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ አገላለጽ/ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)

መንጠቆዎች

ስል እና ቆልመም ያለ ቁራጭ ብረት፣ ወይም ሰዎች አሳ እና በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች እንስሳትን የሚያጠምዱበት እንጨት

ቅርፊት

በአሳ፣ አዞ፣ እና ሌሎች እንስሳት ላይ የሚገኝ ጠንካራ ቁርጥራጭ ቆዳ

የሚያነሳችሁ አይኖርም፣ ወይም ማንም አያነሳችሁም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ በሜዳ/በዱር የሚሞቱ መሆኑን ያሳያል፡፡ "ማንም በድናችሁን አንስቶ ወይም ሰብስቦ አይቀብርም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)