am_tn/ezk/27/34.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ የጢሮስ ከተማ የተሰበረች መርከብ ሆና መገለጽዋ ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ቁጥሮች "አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡

በጥልቁ ውሃ፣ በወንዙ በተንኮታኮትሽ/በጠፋሽበት ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ባህሩ፣ ጥልቁ ውሃ በከደነሽ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መንኮታኮት

"መንኮታኮት" ወደ ቁርጥራጭነት መሰባበር ነው፡፡

ቡድን

በቡድን የሚሰሩ ሰራተኞች

በአንቺ ላይ በደረሰው ደነገጡ

"በአንቺ ላይ በደረሰው ደንግጠውና በፍርሃት ተውጠው ነበር"

ንጉሦቻቸው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ

"ፍርሃት" የሚለው ረቂቅ ስም "በፍርሃት" በሚለው ተውሳከ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ንጉሦቻቸው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ፊታቸው ተንቀጠቀጠ

እዚህ ስፍራ "ፊት/ገጽ" የሚለው የሚወክለው የአንደን ሰው ሁለንትና ነው፡፡ "ይንቀጠቀጡ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንቺ ላይ በአድናቆት አፏጩ

ማፏጨት በጥርስ መሃል የፉጨት ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ በስጋት፣ በሃዘን ወይም በአድናቆት ጊዜ ሊሰማ ይችላል፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ማስፈራሪያ/ለድንጋጤ ሆንሽ

"ፍርሃት" የሚለው ረቂቅ ስም "አሰቃቂ" በሚለው ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አሰቃቂ/አስፈሪ ሆንሽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)