am_tn/ezk/27/28.md

1.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ የጢሮስ ከተማ የተሰበረች መርከብ ሆና መገለጽዋ ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

"አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በባህሩ የሚገኙ ከተሞች ይንቀጠቀጣሉ

እዚህ ስፍራ "በባህሩ የሚገኙ ከተሞች" የሚለው የሚወክለው በእነዚያ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ "በባህሩ በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ/በጭንቀት ይርዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መቅዘፊያውን የሚይዙ ሰዎች በሙሉ

"አስጨናቂዎች ሁሉ"

በምሬት ያለቅሳሉ

"በከፍተኛ ሀዘን ያለቅሳሉ"

በራሳቸው ላይ ትቢያ ይነሰንሳሉ፡፡ በአመድ ላይ ይንከባለላሉ

እነዚህ የሀዘን እና በምሬት የማልቀስ መገለጫዎች ናቸው፡፡ (ትምዕርታዊ/ ምልክታዊ ድርጊቶች የሚለውን ይመልከቱ)