am_tn/ezk/27/24.md

1.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

"አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡

ከአንቺ ጋር የሚነግዱት እነዚህ ነበሩ

"እነርሱ ከአንቺ ጋር ይነግዳሉ"

ባለ ብዙ ጌጥ ሀምራዊና በሚያምሩ ቀለማት ተጠለፉ ልብሶች

"ብዙ ቀላም ያላቸው እና ጌጠኛ ሀምራዊ ልብሶች"

በብዙ ቀለማት ያጌጡ፣ ጥልፎች፣ እና አምረው የተሰሩ ካባዎች

"ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ባለ ብዙ ህብር ካባዎች"

የጢሮስ መርከቦች ነጋዎችሽን ያመላልሱ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የጢሮስ መርከቦች ነጋዴዎችሽን ያጓጉዙ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እጅግ በሀብት በተሞሉ ጭነቶች በልጽገሽ/ተሞልተሸ ነበር

የጢሮስ ብልጽግና የተገለጸው በጭነት እንደተሞላች መርከብ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የባህሮች ልብ

"በባህር መሃል፡፡" ይህ በሕዝቅኤል 27፡4 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡