am_tn/ezk/27/16.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

"አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡

አራም ነጋዴ ነበረች

እዚህ ስፍራ "አራም" የሚለው የሚያመለክተው የአራም ሰዎችን ነው፡፡ "የአራም ሰዎች ነጋዴዎች ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነጋዴ

"በንግድ የተሰማራ"

ብሩህ አረንጓዴ የከበረ ድንጋይ/ዛጎል

እጅግ ውድ የሆነ የከበረ አረንጓዴ ድንጋይ ነው

ሀምራዊ

እዚህ ስፍራ ሀምራዊ ጨርቅ ወይም ሱፍ ክር የሚያመለክተው የዕቃውን ቀለም ነው፡፡ "ሀምራዊ ጨርቅ" ወይም "ሀምራዊ ክር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

ሉል

ነጭ እና ጠንካራ የሆነ በባህር ውስጥ ከሚገኙ ፍጥረቶች የሚገኝ ውብ ዶቃ

ቀይ እንቁ

ቀይ እንቁ፣ ውድ ዋጋ ያለው እጅግ ውድ ድንጋይ

ይሁዳ እና የእስራኤል ምድር ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር

እዚህ ስፍራ "ይሁዳ እና የእስራኤል ምድር" የሚሉት የሚያመለክቱት የእነዚያን ስፍራዎች ሰዎች ነው፡፡ "የይሁዳ እና የእስራኤል ሰዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ/ይነግዱ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሚኒት…ኬልቦን…ዛሐር

እነዚህ የቦታዎች ስሞች ነበሩ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ጣፋጭ/ኬክ

እዚህ ስፍራ "ጣፋጭ/ኬክ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል ትርጉም በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ ሌሎች ትርጉሞች ሌላ አይነት ምግብ አድርገው ሊተረጉሙት ይችላሉ፡፡

እጣን

ጣፋጭ ማዕዛ ያለው ከዛፍ የሚገኝ ሙጫ

የተትረፈረፈ ሀብት

"ብዙ ሀብት" ወይም "ታላቅ ንብረት"