am_tn/ezk/27/06.md

1.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ የጢሮስ ከተማ ውብ መርከብ እንደሆነች ተደርጎ መብራራቱ ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ሀረጋት "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው ጢሮስን የሚገነቡትን ነው፡፡ "የአንቺ" የሚለው ጢሮስን ያመለክታል፡፡

የጀልባ መቅዘፊያዎች

ሰዎች ጀልባ ለመቅዘፍ የሚገለገሉበት ረጅም የሆነ በአንድ ጫፉ ጠፍጣፋነት ያለው እንጨት፡፡

የጀልባ ወለል

ሰዎች ሊራመዱበት የሚችሉት የጀልባዋ ክፍል

እነርሱን ይሸፍናሉ

"ይሸፍኗቸዋል"

ከዝሆን ጥርስ

ነጭ፣ ውብ፣ እና ጠንካራ ከእንስሳ ጥርስ የተሰራ ነገር

የመርከብ ሸራ

ረጅም የሆነ ነፋስ መርከቧን እንዲያንቀሳቅስ የሚያደርግ ሸራ

የመርከቦችሽ ሸራ ቀላማቸው ውብ የሆኑ ከግብጽ በመጣ የሀር ጨርቅ ነው

የመርከቦች ሸራ ከጢሮስ አርማ ወይም ባንዲራ ጋር ተነጻጸሯል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመለከቱ)