am_tn/ezk/27/01.md

2.5 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የነገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የእንጉርጉሮ እርዳታ

"እንጉርጉሮ" የሚለው ይህ ረቂቅ ስም "ለቅሶ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አልቃሽ መሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ለጢሮስ እንዲህ በል

እዚህ ስፍራ "ጢሮስ" የሚለው ቃል በጢሮስ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ "ለጢሮስ ሰዎች አንዲህ በላቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በባህሩ መግቢያ በሮች ለሚኖሩ

"በባህሩ በሮች ለሚኖሩ" ወይም "በባህሩ መግቢያ ለሚኖሩ"

ጢሮስ ሆይ፣ እንዲህ ብለሻል

እዚህ ስፍራ "ጢሮስ" የሚለው ቃል በጢሮስ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ "የጢሮስ ሰዎች፣ እንዲህ ብላችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ በውበት ፍጹም ነኝ

"ውበት" የሚለው ረቂቅ ስም "ውብ" በሚለው ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ ፍጹም ውብ ነኝ" ወይም "ሙሉ ለሙሉ/እንከን የለሽ ውብ ነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)