am_tn/ezk/25/14.md

2.3 KiB

በቀሌን በኤዶም ላይ በህዝቤ በእስራኤል አማካይነት አወርድባቸዋለሁ

እዚህ ስፍራ የእስራኤል "እጅ" የሚለው የእስራኤልን ሰራዊት የሚገልጽ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ያህዌ በኤዶም ህዝብ ላይ በቀል ስለመፈጸም የሚናገረው እንደ ብርድልብስ ሆኖ ቁጣው እንደሚሸፍናቸው አድርጎ ነው፡፡ "በቀል" የሚለው ረቂቅ ስም "ቀጣ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ህዝቤ እስራኤል የኤዶምን ህዝብ እንዲቀጣ እጠቀምበታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በኤዶም ላይ እንደ ቁጣዬ እና ሀይሌ ያደርጉባቸዋል

"ለኤዶማውያን ቁጣዬን እና ሀይሌን ያሳያሉ" ወይም "ኤዶማውያንን እንደ ቁጣዬ እና ሀይሌ ይቀጧቸዋል"

ቁጣዬ እና ሀይሌ

"ሀይል/ንዴት" የሚለው ቃል በመሰረቱ "ቁጣ" የሚለውን ተመሳሳይ ነገር አጠናክሮ ይገልጻል፡፡ "ሀይሌ እና ቁጣዬ" ወይም "እጅግ ከፍ ያለው ቁጣዬ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በቀሌን ያውቃሉ

"በቀል" የሚለው ረቂቅ ስም "ቀጣ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የኤዶም ሰዎች እኔ እንደቀጣኋቸው ያውቃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)