am_tn/ezk/25/12.md

2.3 KiB

ኤዶም ተቀብሏል

እዚህ ስፍራ "ኤዶም" የሚያመለክተው በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ "የኤዶም ሰዎች ተቀብለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳ ቤት

"ቤት" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የይሁዳ ትውልድ የሆኑትን ያመለክታል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የይሁዳ ወገን ህዝብ" ወይም "የይሁዳ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ኤዶምን በእጄ እመታለሁ

እዚህ ስፍራ ያህዌ ህዝቡን በቀጥታ በእጁ እንደሚመታ አድርጎ ይናገራል፡፡ ተመሳሳይ ሆነው ሀረግ በሕዝቅኤል 25፡7 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እኔ ኤዶምን እቀጣለሁ፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከቴምና ጀምሮ እስከ ድዳን…አጠፋቸዋለሁ

"ኤዶምን ከቴምና እስከ ድዳን…አጠፋለሁ፡፡" እነዚህ በኤዶም ሁለት ጫፎች በተቃራኒ አቅጣጫ የሚገኙ ከተሞች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ያህዌ መላዋን ኤዶምን ያጠፋታል ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ ይወድቃሉ

"መውደቅ" የሚለው ቃል የሚወክለው መገደልን ሲሆን "ሰይፍ" የሚለው በጦርነት የሚያጠፏቸውን ጠላቶቻቸውን ያመለክታል፡፡ "ጠላቶቻቸው በሰይፍ ይገድሏቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)