am_tn/ezk/25/08.md

3.7 KiB

ሞአብ እና ሴይር

እነዚህ ስፍራዎች በውስጣቸው የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታሉ፡፡ "የሞአብ እና ሴይር ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ ተመልከቱ! የይሁዳ ቤት እንደ…ነው

"የይሁዳን ቤት ተመልከቱ፡፡ እንደ…ነው"

የይሁዳ ቤት…ነው

"ቤት" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የይሁዳ ትውልድ የሆኑትን ያመለክታል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የይሁዳ ወገን ህዝብ" ወይም "የይሁዳ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ! እኔ እከፍታለሁ

"ተመልከት! እኔ እከፍታለሁ" ወይም "ስማ! እኔ እከፍታለሁ" ወይም "ቀጥሎ ለምናገረው ትኩረት ስጥ! እኔ እከፍታለሁ"

ከከተማው ዳርቻ ጀምሬ፣ የሞአብን ቁልቁለቶች እከፍታለሁ

ይህ ማለት እርሱ ሞአብን ራሷን ለማጥቃት በመጀመሪያ ለታደሮች መንገዱን ለመጥረግ በሞአብ ዳርቻ የሚገኙ ከተሞችን ያጠፋል፡፡ "በድንበሮቿ የሚገኙ ከተሞችን በማጥፋት/በመደምሰስ ወደ ሞአብ የሚወስደውን ጥርጊያ እከፍታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ከተሞች በመጀመር

እዚህ ስፍራ የሞአብ ከተማ የተነገረው ወንዴ በሆነ ተውላጠ ስም "የእርሱ" በሚለው ነው፡፡ "በእርሱ ከተሞች በመጀመር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የቤት የሺሞት፣ በአልሜዎን፣ እና ቂርያትይም

"ከታላቂቆቹ ከተሞች ከቤት የሺሞት፣ አልሜዎን፣ እና ቂርያትይም እጀምራለሁ፡፡" እነዚህ ሶስት ስፍራዎች ከተሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በአሞን ህዝቦች ላይ የተነሱትን የምስራቅ ሰዎች

"አሞንን ያጠቁትን ከምስራቅ ሰዎች የሆኑትን እነዚያኑ ሰራዊት እልካለሁ"

እነርሱን እንደ ንብረት/ሃብት አድርጌ እሰጣለሁ

እዚህ ስፍራ ያህዌ አሞንን ከምስራቅ ለመጣው ሰራዊት እንደ ንብረት አድርጎ አሳልፎ እንደ ሰጠ ይናገራል፡፡ "ሰራዊት እነርሱን እንዲይዝ እፈቅዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም አሞን ሰዎች በአገራት መሃል መታሰቢያ አይኖራቸውም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስለዚህም አገራት የአሞንን ሰዎች አያስታውሱም/ይረሳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)