am_tn/ezk/25/06.md

2.3 KiB

እጃችሁን አጨብጭባችኋል፣ በእግራችሁም መሬቱን መትታችኋል/ደቅታችኋል

እነዚህ ድርጊቶች ብርቱ ስሜትን መግለጫ ናቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰዎቹ ተደስተዋል በእስራኤል ላይ ያላቸውን ንቀትም አሳይተዋል፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጣችሁ በእስራኤል ላይ ያለ ንቀት በሙሉ

እዚህ ስፍራ "የእስራኤል ምድር" የሚለው ሀረግ የሚገልጸው በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ "በእስራኤል በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያላችሁ ጥላቻ ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና የተዘለለ/የተተወ የሚሉትን ይመልከቱ)

እነሆ

"ተመልከቱ" ወይም "ቀጥሎ ለምናገረው ትኩረት ስጡ"

በእጄ አኔ እመታችኋለሁ

"በሀይለኛው እጄ እኔ እመታችኋለሁ" እዚህ ስፍራ ያህዌ ህዝቡን በቀጥታ በእጁ እንደሚመታቸው አድርጎ ይናገራል፡፡ "እኔ እቀጣችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተን ለህዝብ/አገራት ዝርፊያ አድርጌ እሰጣችኋለሁ

"እናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአሞን ሰዎችን ሲሆን ነገር ግን ለምድራቸው እና ሀብታቸውም ደግሞ ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ "ጠላት እንደያሸንፋችሁ ደግሞም ምድራችሁን እና ሀብታችሁን እንዲዘርፍ አደርጋለሁ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተን ከህዝቡ እለያለሁ… ከአገራት መሃል እንድጥጠፉ አደርጋለሁ

በመሰረቱ እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ፤ ከእንግዲህ አገር ሆነው እንደማይቀጥሉ እና ያህዌ የአሞንን ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚያጠፋ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)