am_tn/ezk/25/03.md

4.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ለአሞን ሰዎች ምን መናገር እንዳለበት ያህዌ ለሕዝቅኤል ይነግረዋል፡፡

የጌታ የያህዌን ቃል ስሙ

"ይህን ከጌታ ያህዌ ዘንድ የመጣ መልክዕክት ስሙ"

እናንተ፣ "አሃ!" ብላችኋል

"አዳንቃችኋል፡፡" እዚህ ስፍራ "አሃ" የሚለው ቃል ሰዎች በአንዳች ነገር ደስ ሲሰኙ የሚያሰሙት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰዎች ደስ የተሰኙት በእስራኤል እና ይሁዳ ላይ ክፉ ነገር ስለደረሰ ነው፡፡

መቅደሴ በረከሰ ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጠላት ሰራዊት ባረከሰው ጊዜ በመቅደሴ ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱን በመቃወም …ቤቱን በመቃወም

"በምድሪቱ ላይ.. በቤቱ ላይ"

የይሁዳ ቤት

"ቤት" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የይሁዳ ትውልድ የሆኑትን ያመለክታል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የይሁዳ ወገን ህዝብ" ወይም "የይሁዳ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

"ተመልከቱ" ወይም "ቀጥሎ ለምናገረው ትኩረት ስጡ"

በምስራቅ ለሚኖሩ ሰዎች ርስታቸው አድርጌ እሰጣችኋለሁ

ይህ የሚናገረው የአሞንን ምድር የሚወረው እና የምድሪቱን ሀብት እንደዚሁም በላይዋ የሚገኘውን ነገር ሁሉ የሚወስደው የጠላት ሰራዊት የአሞንን ህዝብ ርስቱ አድርጎ እንደወሰደ እንደሚቆጠር አድርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ የጠላት ሰራዊት የአሞንን ህዝብ ባሪያ እንደሚያደርግ አያመለክትም፡፡ "ከእናንተ በስተ ምስራቅ የሚመጣ ሰራዊት እንዲወራችሁ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእናንተ ላይ ይሰፍራሉ፤ ደግሞም በመሃላችሁ ድንኳናቸውን ይጥላል

"ድንኳን ጥለው በአገራችሁ ይኖራሉ"

የምድራችሁን ፍራፍሬ ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ

የፍራፍሬውን እና ወተቱን መገኛ ለይቶ መናገር ሊጠቅም ይችላል፡፡ "ከዛፎቻችሁ ፍሬዎችን ይበላሉ የከብቶቻችሁን ወተት ይጠጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የአሞን ሰዎች የመንጋ መሰማሪያ

እዚህ ስፍራ "የአሞን ሰዎች" የሚለው የሚያመለክተው የአሞን ሰዎችን ምድር ነው፡፡ እንደዚሁም በዚህ ሀረግ መነሻ ላይ በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው መረጃ ሊጨመር ይችላል፡፡ "የቀረውን የአሞን ሰዎች ምድር የመንጋ መሰማሪያ አደርገዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና የተዘለለ/የተተወ የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ ይህንን ሲናገር ሰዎች እርሱ ያህዌ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)