am_tn/ezk/25/01.md

2.4 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ወደ አሞን ሰዎች ፊትህን አዙር

አሞን ሩቅ ስፍራ ነበር፣ ስለዚህ ሕዝቅኤል በዚያ የሚገኙ ሰዎችን ማየት አይችልም፣ ነገር ግን ወደዚያ አቅጣጫ መመልከት ያንን ህዝብ የመጉዳት ምልክት ይሆናል፡፡ በሕዝቅኤል 6፡2 ላይ የሚገኘው ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ወደ አሞን ህዝብ ዞረህ ተመልከት" ወይም "በዚያ ያለው ህዝብ ጥፋት እንዲደርስበት ወደ አሞን አቅጣጫ ተመልከት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/መልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የአሞን ህዝብ

"የአሞን ትውልድ" ወይም "በአሞን ምድር የሚኖሩ"

በእነርሱ ላይ ትንቢት ተናገር

"በእነርሱ ላይ ስለሚደርስባቸው ክፉ ነገሮች ትንቢት መናገር፡፡" ይህ ማለት በአሞን ሰዎች ላይ ስለሚደርስ አስከፊ/አስጨናቂ ነገሮች ትንቢት መናገር ማለት ነው፡፡ በሕዝቅኤል 4፡7 ላይ የሚገኘው ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡