am_tn/ezk/24/25.md

3.3 KiB

የምይዘው መቅደሳቸው

እዚህ ስፍራ ያህዌ ቤተመቅደሳቸውን መደምሰሱን እንደሚይዘው አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ "ቤተመቅደሳቸውን እኔ እደመስሰዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ደስታቸው እና ኩራታቸው የሆነውን

"ደስታ/ሀሴት" እና "ኩራት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በስማዊ ሀረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ደስታ የሚያደርጉበት እና የሚኮሩበት/የሚመኩበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስደተኛ

በጦርነት ወይም በሌላ ጥፋት መከራ ምክንያት አገራቸውን ለቀው ለመሄድ የተገደዱ

አፎቻችሁ ይከፈታሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ሕዝቅኤል የተሰጠው መረዳት እና የመናገር ችሎታ በአፉ መከፈት ተገልጽዋል፡፡ "እኔ አፍህን እከፍተዋለሁ" ወይም "መናገር የሚገባህን ታውቃለህ" ወይም "ምን መናገር እንዳለብህ እንድታውቅ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ ትናገራለህ - ከእንግዲህ ወዲያ ዝም አትልም

እነዚህ ሁለቱም ሀረጎች ሕዝቅኤል ይናገራል የሚለውን ይገልጻሉ፡፡ መናገሩ እንደማይቀር ትኩረት ለመስጠት በሁለተኛው ሀረግ በአሉታ ተገልጽዋል፡፡ (ምጽት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእነርሱ ምልክት ትሆናለህ

እዚህ ስፍራ "ምልክት" የሚለው ቃል ለሚመለከቱት ልዩ ማስጠንቀቂያ እንደሚያስተላልፍ ያመለክታል፡፡ ያህዌ ሕዝቅኤልን እና ድርጊቱን እንደዚህ ማስጠንቀቂያ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ዘይቤ በሕዝቅኤል12፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "አንተ ለእነርሱ ማስጠንቀቂያ ትሆናለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ ይህንን ሲናገር ሰዎች እርሱ ያህዌ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)