am_tn/ezk/24/22.md

1.6 KiB

ትቀልጣላችሁ

እዚህ ስፍራ "መቅለጥ" የሚለው እየሟሸሹ መምጣትንና መሞትን የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ "በጣም ትከሳላችሁ ደግሞም ቀስ በቀስ ትሞታላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በኃጢአታችሁ/በበደላችሁ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር የእነዚህን ሰዎች ኃጢአት ይቅር እንደማይል ነው፡፡ "ኃጢአታችሁን ይቅር አልልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ማቃሰት

ይህ እርዳታ የሚፈልግ እና በብዙ ስቃይ ውስጥ የሚገኝ መናገር ያቃተው ሰው የሚያሰማው ድምጽ ነው፡፡

ስለዚህም ሕዝቅኤል ለእናንተ ምልክት ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ምልክት" የሚለው ቃል ለሚመለከቱት ሰዎች ልዩ ማስጠንቀቂያ የሚያስተላልፍን ነገር ያመለክታል፡፡ ያህዌ ስለ ሕዝቅኤል እና የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደዚህ ማስጠንቀቂያ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ዘይቤ በሕዝቅኤል 12፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ስለዚህም ሕዝቅኤል ለእናንተ ማስጠንቀቂያ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)