am_tn/ezk/24/19.md

3.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

የእስራኤል ሰዎች ሕዝቅኤልን ይጠይቁታል፣ሕዝቅኤል ደግሞ ያህዌ ለእነርሱ የተናገረውን ይነግራቸዋል፡፡

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ሲሆን በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያቆብ ትውልድ የሆኑትን እስራኤላውያንን ያመለክታል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

እዚህ ስፍራ "እነሆ" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው መረጃ ንቁ ሆነን እንድንጠብቅ ያደርጋል፡፡

የነፍሳችሁን ኩራት… ቤተመቅደስን አረክሳለሁ - ደግሞም ልጆቻችሁ

"የነፍሳችሁ… ኩራት የሆነውን ቤተ መቅደሴን አረክሳለሁ፡፡ ልጆቻችሁ…"

የሃይላችሁ ኩራት

ይህ የሚገልጸው የቤተመቅደሱ ህንጻ ህዝቡ የሚኮራበት ነገር መሆኑን ነው፡፡ ይህ የተገለጸው ለኩራታቸው መነሻ ከመሆን አልፎ "ኩራታቸው" እንደሆነ ነው፡፡ "የምትመኩበት/የምትኮሩበት ህንጻ" ወይም "የብርቱ ኩራታችሁ ምክንያት/መገኛ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የዐይኖቻችሁ ምቾት

እዚህ ስፍራ ያህዌ ህዝቡን የገለጸው "በዐይኖቻቸው" ነው፡፡ "ዐይኖቻችሁን ልታሳርፉባቸው የምትወዷቸው ህንጻዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የነፍሳችሁ ናፍቆት

እዚህ ስፍራ ያህዌ ለውስጣዊ ስሜታቸው ትኩረት በመስጠት ህዝቡን የሚገልጸው "በነፍሳቸው" ነው፡፡ "በእርግጥ የምትወዱት ህንጻ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችሁ… በሰይፍ ይወድቃሉ

ይህ ጠላቶቻቸውን በሰይፎቻቸው ይገልጻል፡፡ "ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችሁ… በጦርነት ይገደላሉ" ወይም "ጠላቶቻችሁ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችሁን… በሰይፍ ይገድላሉ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)