am_tn/ezk/24/15.md

2.6 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የዐይኖችህ መሻት ከ…

ይህ የሚያመለክተው የሕዝቅኤልን ሚስት ነው፡፡ ያህዌ ሕዝቅኤልን ሚስቱን በሚመለከትበት የሰውነቱ ክፍል ያመለክታል፡፡ "ከ…በጣም የምትወዳት፣ ሚስትህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በመቅሰፍት

"በበሽታ"

ማዘን ወይም ማልቀስ የለብህም፣ እምባህ መፍሰስ የለበትም

እነዚህ ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጣሉ፤ ትኩረት የሚሰጡት ሕዝቅኤል ሚስቱ በሞተች ጊዜ ማልቅስ እንደሌለበት ነው፡፡ "ማዘን ወይም ማልቀስ የለብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞተው/ራሳው

ይህ የሚያመለክተው የሞተችውን ሚስቱን ነው፡፡ "የሞተችው ሚስትህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

ጥምጥም

በጭንቅላት ላይ የሚጠቀለል ከረጅም ጨርቅ የተሰራ የራስ መሸፈኛ

ነጠላ ጫማ/ሰንደል

በቁርጭምጭሚት ዙሪያ ማሰሪያ ያለው የሚጫሙት ቀላል ጫማ፡፡

የፊትህን ጸጉር/ጺምህን አትሸፍን

በእስራኤል ወንዶች ሀዘናቸውን ለመግለጽ ጺማቸውን ይላጫሉ፣ ከዚያም ጺማቸው መልሶ እስኪበቅል ድረስ ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡ ያህዌ ሕዝቅኤልን ጺሙን እንዳይሸፍን አዘዘው፤ ይህም ሀዘኑን ለመግለጽ ጺሙን አለመላጨቱን ለማሳየት ነው፡፡ "ጺምህን በመሸፈን አታልቅስ" ወይም "ጺምህን በመላጨት እና በመሸፈን አትዘን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)