am_tn/ezk/24/14.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በምሳሌ ኢየሩሳሌምን ስለሚወክል የማብሰያ ማሰሮ ይናገረዋል፡፡ ይህ ምሳሌ እስከዚህ ቁጥር መጨረሻ ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች/በምሳሌ መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

አሊያም ይህን ከማድረግ አላርፍም/አላቆምም

"አሊያም እናንተን ከመቅጣት አላርፍም፡፡" እዚህ ስፍራ "ይህን" የሚለው የሚያመለክተው ያህዌ ህዝቡን መቅጣቱን ነው፡፡

እንደ መንገድሽ እና እንደ ስራሽ ይከፍሉሻል/ይፈርዱብሻል

ይህ የሚገልጸው ያህዌ ህዝቡን የሚቀጣው/የሚፈርድባቸው በመንገዳቸው ምክንያት ሲሆን፤ "መንገዳቸው" ራሱ እንደሚፈርድባቸው አድርጎ ነው፡፡ "በተግባራችሁ እና በመንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ ያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው

ያህዌ የተናገረውን እርግጠኝነት ለማጽናት በራሱ ይምላል/ በስሙ ይምላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህ ነው" ወይም "እኔ፣ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)