am_tn/ezk/24/07.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በምሳሌ ኢየሩሳሌምን ስለሚወክል የማብሰያ ማሰሮ ይናገረዋል፡፡ ይህ ምሳሌ እስከ ሕዝቅኤል 24፡14 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች/በምሳሌ መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሷ ደም በመሀሏ ነው

ይህ ማለት በኢየሩሳሌም የተገደሉት ሰዎች ደም እስከ አሁን በዚያ አለ፡፡ "ከእርሷ መሃል የተገደሉት ሰዎች ደም እስከ አሁን በዚያ አለ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሷ

"የእርሷ" የሚለው ቃል፣ በማብሰያ ማሰሮ የተገለጸችውን ኢየሩሳሌምን ያመለክታል

በአፈር እንዲሸፈን በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም፣ ነገር ግን በጠፍጣፋው አለት ላይ አደረገችው

ይህ ኢየሩሳሌምን ሰዎችን እንደገደለች እና ደማቸውንም የት ማፍሰስ እንደመረጠች አድርጎ በሰውኛ ይገልጻታል፡፡ "የተገደሉት በጠፍጣፋ አለት ላይ እንጂ፣ ደማቸውን ሊደብቅ በሚችል በአፈር ላይ አልነበረም" ወይም "ደማቸው በጠፍጣፋ አለት ላይ እንጂ አፈር ሊሸፍነው በሚችለው ስፍራ ላይ አልፈሰሰም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስወኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጠፍጣፋ አለት ላይ አፈሰሰችው

"ደማቸውን በገላጣ አለት ላይ አፈሰሰች"

ስለዚህም ቁጣዬን ለበቀል አነሳሳች

እዚህ ስፍራ ያህዌ ራሱ በኢየሩሳሌም ሰዎችን በገደሉ ላይ በቀልን ስለመውሰዱ ይናገራል፡፡ "እኔ ራሴ ተመልክቼ በቁጣዬ እበቀል ዘንድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም መሸፈን አይችል ዘንድ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስለዚህም ምንም ይሸፍነው ዘንድ እንዳይችል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)