am_tn/ezk/24/06.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በምሳሌ ኢየሩሳሌምን ስለሚወክል የማብሰያ ማሰሮ ይናገረዋል፡፡ ይህ ምሳሌ እስከ ሕዝቅኤል 24፡14 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች/በምሳሌ መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የደም ከተማ

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚያመለክተው "ግድያን" ነው፡፡ "የነብሰ ገዳዮች ከተማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማብሰያ ማሰሮ

ያህዌ ኢየሩሳሌምን ከማብሰያ ማሰሮ ጋር ማነጻጸሩን ይቀጥላል፡፡ "እንደ ማብሰያ ማሰሮ ናት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዝገት

በብረት ላይ የሚገኝ ቀላ ያለ ነገር፡፡ ዝገት ብረትን በመብላት ቀስ በቀስ ያጠፋዋል፡፡

ጥቂት በጥቂቱ ውሰድ

ያህዌ ይህንን ትዕዛዝ ለአንድ የተወሰነ ሰው አልሰጠም፡፡ ይህ በዚህ ዘይቤያዊ አነጋገር ለአንድ የተወሰነ ሰው ያልተሰጠ አጠቃላይ ትዕዛዝ ነው፡፡

ዕጣ አትጣል፣ ሁሉንም አውጣ

ዕጣ መጣል/ማውጣት የትኛው ቁራጭ ስጋ እንደሚወጣ የመምረጫ መንገድ ነበር፣ ነገር ግን ያህዌ ሁሉም ቁርጥራጭ ስጋ እንዲወጣ ስለፈለገ ዕጣ መጣል አላስፈለገም፡፡