am_tn/ezk/24/03.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በምሳሌ ኢየሩሳሌምን ስለሚወክል የማብሰያ ማሰሮ ይናገረዋል፡፡ ይህ ምሳሌ እስከ ሕዝቅኤል 24፡14 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች/በምሳሌ መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ አመጸኛ ቤት

ይህ በቤቱ ውስጥ ስለሚኖር ቤተሰብ፣ በዚህ ሁኔታ ለዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ስለሆነው ስለ እስራኤል የተነገረ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡5 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ይህ አመጸኛ ህዝብ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቅንጥብጣቢውን ምግብ ሰብስቡ

እዚህ ስፍራ "ምግብ" በተለይ የሚያመለክተው ስጋን ነው፡፡ "ቅንጥብጣቢውን ስጋ አስቀምጡ" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከመንጋው ምርጡን

እዚህ ስፍራ "መንጋ" የሚያመለክተው በጎችን ነው፣ የወፍ መንጋን አይደለም፡፡

ከስሩ የአጥንት ክምር

በአንዳንድ ባህል ከእንጨት ይልቅ አጥንት ረጅም ጊዜ መንደድ ስለሚችል እሳት ውስጥ አጥንት ይጨምራሉ፡፡ ይህ የሚገልጸው ምርጥ የሆኑት አጥንቶች በማሰሮ ውስጥ ከተጨመሩ በኋላ የሚቀሩትን አጥንቶች ነው፡፡ "የተቀሩትን አጥንቶች እሳቱን ለማቀጣጠል ከማሰሮው ስር ጨምር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)