am_tn/ezk/24/01.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ሕዝቅኤልን እንዲህ አለው/ተናገረው

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነብዩ ወይም ለህዝቡ አዲስ ነገርን ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዘጠነኛው አመት

"በ9 ነኛው አመት፡፡" ይህ የሚያመለክተው በንጉሥ ኢዮአቄም አገዛዝ ስር ለምን ያህል ጊዜ በስደት እንደቆዩ ነው፡፡ "በንጉሥ ኢዮአቄም ስደት በዘጠነኛው አመት" (ተከታታ ቁጥሮች እና (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ))

አስረኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን

"በአስረኛው ወር በወሩ በአስረኛው ቀን" ወይም "በ10ኛው ወር በ10ኛው ቀን፡፡" ይህ በዕብራውያን ዘመን አቆጣጣር አስረኛው ወር ነው፡፡ (የዕብራውያን ወሮች እና ተከታታ ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር"

የባቢሎን ንጉሥ ከቧታል

የባቢሎን ሰራዊት የተገለጸው በመሪው ነው፡፡ "የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ከቧታል" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)