am_tn/ezk/23/43.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ዳግም የኢየሩሳሌም እና የሰማርያ ከተሞችን ሁለት ዘማዊያን እንደሆኑ አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተተወችው እርሷ…ከእርሷ ጋር፣ ደግሞም እርሷ ከእነርሱ

ይህ የሚያመለክተው ከሁለቱ እህትማማቾች አንዷን ሲሆን ነገር ግን ሁኔታው ማናልባት ለሁለቱም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡ በቋንቋችሁ አንደኛው እህት ተለይታ መገለጽ ካለባት ኦሖሊባን ጥቀሱ፡፡

እነርሱ ወደ እርሷ ሄደው ወንዶች ወደ ዘማዊት ሴት እንደሚሄዱ ከእርሷ ጋር ተኙ

ይህ የሚያነጻጽረው ወንዶች ከዘማዊት ሴት ጋር እንደሚተኙ በዚያው መንገድ ከእርሷ ጋር ማድረጋቸውን ነው፡፡ "ወንዶች ከዘማዊት ሴት ጋር እንደሚተኙበት መንገድ ከእርሷ ጋር ተኙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እርሷ ሄዱ/ገቡ

"እርሷ ወደ ነበረችበት ስፍራ ሄዱ" ወይም "ወደ እርሷ ሄዱ"

በዚህ መንገድ ከኦሖላ እና ከኦሖሊባ ጋር ተኙ

"ከኦሖላ እና ከኦሖሊባ ጋር የተኙት እንደዚህ ነው"

ፍርድ ስጥ/አሳልፍ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ኮንን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ደም ያፈሰሱ…ደም በእጃቸው አለ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ሰዎችን የገደሉ…ነብሰ ገዳዮች" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)