am_tn/ezk/23/38.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና የሰማርያ ሰዎች እንዴት ለእርሱ ታማኞች እንዳልሆኑ ይናገራል፡፡

መርከስ/ንጹህ አለመሆን

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ነገር ንጹህ አድርጎ የማይቆጥረው ወይም የረከሰ ሰው በአካል እንደቆሸሸ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ ይህ ስም በሕዝቅኤል 23፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰንበቴን ባረከሱበት በዚያው ቀን

"በዚያው ቀን" የሚለው ሀረግ "ቤተ መቅደሴን አረከሱ" የሚለውን የቀደመውን ሀረግ ያመለክታል፡፡ "ቤተ መቅደሴን ባረከሱበት በዚያው ቀን ሰንበቴንም አረከሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

"ትኩረት ስጡ፣ ምክንያቱም ቀጥሎ የምናገረው እውነተኛ እና ጠቃሚ ነገር ነው"

በቤቴ መሃል

ይህ በአጠቃላይ ቤቱን ያመለክታል፡፡ "መሃል" የሚለው ትኩረት የሚሰጠው የተደረገው የሆነው በግልጽ በቤተ መቅደስ ሲሆን መላውን ስፍራ አርክሷል፡፡ "በቤቴ/በራሴ ቤት" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)