am_tn/ezk/23/36.md

1.5 KiB

የሰው ልጅ፣ በኦሖላ እና ኦሖሊባ አትፈርድምን?

ያህዌ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ለሕዝቅኤል እንደ ተሰጠ ትዕዛዝ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ የኢየሩሳሌም እና የሰማርያ ከተሞች በኦሖላ እና ኦሖሊባ ተወክለዋል፡፡ "የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሖላ እና ኦሖሊባ አትፈርድም!" ወይም "የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሖላ እና ኦሖሊባ በተወከሉት በእነዚያ ሁለት ከተሞች ህዝቦች ላይ ፍረድ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በእጆቻቸው ላይ ደም አለ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "እነርሱ ሰዎችን ገድለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)