am_tn/ezk/23/33.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በስካር እና በሀዘን ትሞያለሽ

ይህ ጠጪነት እና ሀዘን ሰውነቷን እንደተቆጣጠረው አድርጎ በጣም ጠጪ እና ሀዘንተኛ ስለመሆን ይናገራል፡፡ "በጣም ሰካራም እና ሀዘንተኛ ትሆኛለሽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የፍራቻ እና የጥፋት ጽዋ

"ፍራቻ እና ጥፋት የሚያስከትል ጽዋ፡፡" እዚህ ስፍራ "ፍራቻ" እና "ጥፋት" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ቅጣቷ ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "በዚያ ጽዋ ውስጥ የሚገኘው ፍራቻን እና ጥፋትን ያስከትላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የእህትሽ የሰማርያ ጽዋ

የኦሖሊባ እህት የሆነችው ኦሖላ የምትወክለው ሰማርያን ነው፡፡ ሰማርያ የተጠራችው በስሟ ነው፤ ነገር ግን እንደ እህት ተጠቅሳለች፡፡ ጽዋው እርሷ ለምትቀበለው ቅጣት ምልክት ነው፡፡ "ይህ ሰማርያን የምትወክለው እህትሽ የምትጠጣው ራሱ ያው የቅጣት ጽዋ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጡቶችሽን ብጪ

"ጥቶችሽን ቁረጪ"

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ/አዋጅ ነው

ያህዌ ስለሚያዘው/አዋጁ እርግጠኝነት ለመናገር በራሱ ይምላል/በስሙ ያውጃል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የጌታ የያህዌ አዋጅ ይህ ነው" ወይም "እኔ፣ ጌታ ያህዌ ያወጅኩት/ቃሌ ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)