am_tn/ezk/23/32.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንቺም የእህትሽን ጽዋ ትጎነጫለሽ/ትጠጫለሽ

እዚህ ስፍራ ያህዌ ቅጣትን ሴቲቱ የምትጠጣው የወይን ጽዋ አድርጎ ይናገራል፡፡ "እንደ እህትሽ አንቺም ተመሳሳይ የቅጣት ጽዋ ትጠጫለሽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእህትሽ ጽዋ ይኸውም

እዚህ ስፍራ "ጽዋው" የሚወክለው በጽዋው ውስጥ የሚገኘውን ነው፡፡ "ከእህትሽ ጽዋ ይኸውም" ወይም "በእህትሽ ጽዋ ውስጥ ሚገኘውን ሁሉ፣ ደግሞም የእርሷ ጽዋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መሳቂያ… መሳለቂያ

እነዚህ ሁለቱም ሀረጎች ከሞኝነት ባህሪው የተነሳ የሚሳቅበት እና የሚተች ሰው ባህሪን ያመለክታሉ፡፡ መናቅ በአንድ ነገር ወይም በአንድ ሰው ላይ ማፌዝ ወይም ማወረድ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ጽዋ ብዙ መጠን ይይዛል

ይህ ዐረፍተ ነገር በጽዋው ውስጥ የሚገኘው አይልም ምክንያቱም ሕዝቅኤል 23 31 ላይ ያለውን በማንበብ ይታወቃል፡፡ "ይህ ጽዋ ብዙ መጠን ያለው ቅጣት ይዟል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)