am_tn/ezk/23/30.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ነገሮች በድርጊቶችሽ በአንቺ ላይ ይፈጸሙብሻል

"እነዚህ ነገሮች በአንቺ ላይ ከድርጊትሽ የተነሳ ይፈጸምብሻል" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነዚህ ነገሮች በአንቺ ላይ ይሆናሉ ምክንያቱም አንቺ የፈጸምሽው አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ አመንዝራ ማድረግ፣ ህዝቦችን ተከትሎ ማመንዘር

ሕዝቅኤል ይሁዳን ስለምትወክለው (ሕዝቅኤል 23፡4) ኦሖሊባ፣ ለገንዘብ ስትል ከተለያዩ አገራት ህዝቦች ወንዶች ጋር እንደምትተኛ ሴት አድርጎ ይናገራል፡፡ ሕዝቅኤል፣ የይሁዳ ሰዎች የሌሎችን አገራት ሀብት እና ሀይል ለማግኘት ሲሉ የእነርሱን አማልክት በማምለካቸው ምክንያት ያህዌ እንደሚቀጣቸው እንዲያውቁ ይፈልጋል፡፡ "ከሌሎች አገራት ወንዶች ጋር በመዘሞት እንደ አመንዝራ ሴት ይፈጽማሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በጣኦቶቻቸው ረከሰች

ጣኦትን በማምለክ ረከሰች፡፡ "ጣኦቶቻቸውን በማምለክ ረከሰች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መርከስ/ንጹህ አለመሆን

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ነገር ንጹህ አድርጎ የማይቆጥረው ወይም የረከሰ ሰው በአካል እንደቆሸሸ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ ይህ ስም በሕዝቅኤል 23፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስዚህ የእርሷን የቅጣቷን ጽዋ በእጅሽ አስጨብጥሻለሁ

ይህ የሚያመለክተው ኦሖሊባ የምትቀበለው ቅጣት የወይን ጽዋ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "ስለዚህ እህትሽ በተቀጣችበት ተመሳሳይ መንገድ እንድትቀጪ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)