am_tn/ezk/23/28.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

"ትኩረት ስጡ፣ ምክንያቱም ቀጥሎ የምናገረው እውነተኛ እና ጠቃሚ ነገር ነው"

ለምትጠሏቸው እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ…አምልጣችኋቸው ለነበሩት እጅ መልሼ እሰጣችኋለሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይህ ማለት ያመነዝሩባቸው በነበሩ ሰዎች ይያዛሉ፡፡ "የምትጠሏቸው እና ከእጃቸው አምልጣችሁ የነበሩት መልሰው እንዲይዟችሁ እፈቅዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እጃቸው

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል መቆጣጠርን/መልሶ መያዝን ያመለክታል፡፡ "በቁጥጥራቸወ ስር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርቃን እና መራቆት

እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ሙሉ ለሙሉ እርቃን መቅረቷን ትኩረት ይሰጣል፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እርቃንሽ አይሸፈንም

x