am_tn/ezk/23/26.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከግብጽ ምድር

ይህ የሚያመለክተው ዘማዊነቷ ከግብጽ እንደ ጀመረ ነው፡፡ "በግብጽ ምድር የጀመርሽው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እነርሱ ዐይኖችሽን በምኞት አታነሽም

ይህ አንድ ነገር ለመመልከት ጭንቅላታቸውን የሚያዞሩ ሰዎችን ለማመልከት የሚውል መንገድ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ መመልከት የሚወክለው ፍላጎትን ነው፡፡ "በምኞት ወደ እነርሱ አትመለከችም" ወይም "እነዚህን መገሮች አትፈልጊም/አትመኚም" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ግብጽ አታስቢም

እዚህ ስፍራ "ግብጽ" የምትወክለው በግብጽ ውስጥ ያደረገቻቸውን አሳፋሪ ነገሮች ነው፡፡ "ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ውስጥ ያደረግሻቸውን ነገሮች አታስቢም" ወይም "ከዚህ በኋላ በግብጽ ያደረግሽውን አታስቢም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)