am_tn/ezk/23/24.md

3.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንቺ ላይ ይመጡብሻል

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ጥቃት ያደርሱብሻል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መሳሪያ ይዘው

እዚህ ስፍራ "መሳሪያ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል የተለመደ አይደለም፡፡ በርካታ ዘመናዊ ትርጉሞች በዚህ መንገድ ይተረጉሙታል፣ ሆኖም ግን አንዳንድ ቅጂዎች ይህንን ሀረግ ያስወጡታል፡፡

ትላልቅ ጋሻዎችን፣ ትንንሽ ጋሻዎችን፣ እና የወታደር ቆቦችን በዙሪያሽ ሁሉ ያመጣሉ

እነዚህ የመከላከያ ዕቃዎች የተለያዩ የወታደር ክፍሎችን ለማመልከት ያገለግላሉ፡፡ "ትላልቅ ጋሻዎችን፣ ትንንሽ ጋሻዎችን የያዙ እና ቆብ የደፉ ወታደሮች ጥቃት ያደርሱብሻል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንቺ ላይ የቅናቴን ቁጣ አመጣለሁ፣ በሀይል ይነሱብሻል

እዚህ ስፍራ ያህዌ ወታደሮች እንዲያጠቋቸው የሚፈቅደው በእነርሱ ላይ ስለተቆጣ ሲሆን ቁጣውም ተገለጸው በላያቸው እንዳስቀመጠው ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "በእናንተ በጣም ስለቀናሁ፣ በሀይል እንዲያጠቋችሁ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አፍንጮቻችሁን እና ጆሮቻችሁን ይቆርጣሉ

ይህ በባቢሎን ውስጥ ያገባች ሴት ስታመነዝር የሚደርስባትን ቅጣት የሚገልጽ ነው፡፡ "አፍንጫሽን እና ጆሮዎችሽን በመቁረጥ እንደ ዘማዊ ሴት ይቀጡሻል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቀሩት ሰዎችሽ በሰይፍ ይወድቃሉ

"መውደቅ" የሚለው ቃል "መሞት" ለሚለው ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት ሲሆን፤ "ሰይፍ" የሚለው ቃል በሰይፍ ለሚገድሉ ወታደሮች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

የቀሩት ሰዎችሽ/ትሩፋኑ በእሳት ይበላሉ

ይህ ትሩፋኑ በእሳት እንደሚቃጠሉ ይገልጻል፤ እዚህ ስፍራ እሳት እንደሚያጠቃቸው እና እንደሚበላቸው እንስሳ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በህይወት የተረፉት በእሳት ይቃጠላሉ" ወይም "እሳት በህይወት የተረፉትን ያቃጥላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)