am_tn/ezk/23/22.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

"አድምጡ!" እዚህ ስፍራ "እነሆ!" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስደናቂ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል፡፡

በአንቺ ላይ ከየስፍራው እነርሱን አስነሳብሻለሁ

"ከሁሉም አቅጣጫ እንዲነሱብሽ አደርጋለሁ"

ከእነርሱ ጋር ባቢሎናውያንን እና ከለዳውያንን፣ የፋቁድ፣ ሱሔ፣ እና ቆዓ እንደዚሁም አሶራውያንን ሁሉ

ይህ የሚያመለክተው በእነዚህ ስፍራዎች የሚኖሩትን ህዝቦች ሁሉ ሳይሆን፤ ነገር ግን የእነዚህ ስፍራዎችን ወታደሮች ነው፡፡ " ከእነርሱ ጋር የባቢሎን እና የከለዳውያን፣ የፋቁድ፣ ሱሔ፣ እና ቆዓ እንደዚሁም የአሶር ወታደሮችን ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ፋቁድ፣ ሱሔ፣ እና ቆዓ

እነዚህ ባቢሎን ውስጥ የሚገኙ ቦታዎች ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ስፍራዎች ከዚያ አስፍራ የመጡ ወታደሮችን ይገልጻሉ፡፡ " ከፋቁድ፣ ሱሔ፣ እና ቆዓ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ሁሉም ፈረስ ጋላቢ የሆኑ… ጠንካራ፣ ውብ ወንዶች፣ ገዢዎች እና አዛዦች

ይህ ከአሶር የመጡ ኦሖላ አብራቸው የተኛቻቸው አሁን ግን በእርሷ ላይ የተነሱባትን ወንዶች መግለጫ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 23፡6 ላይ ከተሰጠው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡