am_tn/ezk/23/16.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምንዝርናዋ መኝታ

ይህ የሚያመለክተው ከወንዶች ጋር ያመነዘረችበትን ስፍራ እና የዝሙት ተግባሯን ነው፡፡ "ያመነዘረችበት መኝታ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መርከስ/ንጹህ አለመሆን

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ነገር ንጹህ አድርጎ የማይቆጥረው ወይም የረከሰ ሰው በአካል እንደቆሸሸ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ ይህ ስም በሕዝቅኤል 23፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም ራሷን ከእነርሱ ዘወር አደረገች

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ስለዚህም እነርሱን ተወች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)